የአርጀንቲና ድል እና የፎክላንድ ደሴት

0
144
በ1982 ዓ.ም 74 ቀን የፈጀ ጦርነት ያደረጉት አርጀንቲና እና እንግሊዝ ጦርነቱ ያለ አሸናፊ ቢጠናቀቅም በርካታ ወታደሮች ከሁለቱም ወገን ተሰውተዋል።
በ1986 ዓለም ዋንጫ ዲያጎ ማራዶና እንግሊዝ ላይ ሁለት ግቦችን አስቆጥሮ እንግሊዝን ከውድድር ውጭ ሲያደርጋት የፎክላንድ ደሴት ነዎሪዎች ደስታቸውን ገልጸው እንደነበር በታሪክ ይታወሳል።
አብዛኞቹ የፎክላንድ ደሴት ነዎሪዎች እንግሊዝኛ ተናጋሪ ይሁኑ እንጅ አርጀንቲናዊ ስሜት ያላቸውም እንደኾኑ ይነገራል። ከ3ሺህ 685 የማይበልጡ ነዋሪዎች ያሏት የፎክላንድ ደሴት በአሳ ምርቷ እና ወደ ውጭ በምትልከው የበግ ጸጉር ምርቷም ከፍተኛ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ናት።
በነገራችን ላይ የአንድ የፎክላንድ ደሴት ነዋሪ ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢ 113 ሺህ ዶላር በላይ ነው።
ከአርጀንቲና 480 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው የፎክላንድ ደሴት 700 የሚኾኑ ትንንሽየ ደሴቶች ተዋህደው የፈጠሯት ራስ ገዝ ደሴት እንደኾነች ይነገራል።
በደቡብ አሜሪካ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን በኀይል ተቆጣጥራ የነበረችው እንግሊዝ የስፔን ቀኝ ግዛት የነበረችውን አርጀንቲናን በቀኝ ግዛት መቆጣጠር ባለመቻሏ አልፋ የፎክላንድ ደሴቶችን በመውረሯ እና በማሥተዳደሯ የግዛት ይገባኛል ጥያቄው ተፋፍሞ ከአርጀንቲና ጋር ጦርነት የገባችበት ምክንያት እንደኾነ ይነገራል።
በትናንትናው ምሽት ጨዋታ አርጀንቲና እንግሊዝን ማሸነፏን ተከትሎ የአርጀንቲና ተጫዋቾች የፎክላንድ ደሴቶችን ስም እየጠሩ መሰማታቸው በፊፋ ውድድሮች ላይ ፖለቲካዊ ሀሳብ ማንጸባረቅ በሚለው ሕግ ቡድኑ ቅጣት ይጠብቀዋል ተብሏል።
በ2002 የዓለም ዋንጫ እንግሊዝ አርጀንቲናን 1ለ 0 ስታሸንፍ የፎክላንድ ደሴቶች ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳ ነበር። የ1986 የዓለም ዋንጫም አርጀንቲናውያን በልጃቸው ማራዶና አማካኝነት ባስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች ከውድድሩ እንግሊዝ ስትሰናበት በተመሳሳይ የደሴቲቱ ጉዳይ ዋነኛ ትኩረት ነበር።
በ1982 እና በዘንድሮው በ2026 የዓለም ዋንጫም ሁኔታው ትኩረት ማግኘቱ አልቀረም። የሁለቱ ሀገራት የውዝግብ መነሻ የኾነችው የፎክላንድ ደሴት ጉዳይ ትኩረትን እንደሳበ ልክ እንደ 1986ቱ የዓለም ዋንጫ ሁሉ አርጀንቲና ውድድሩን በበላይነት ታጠናቅቅ ይኾን? የሚለው ጉዳይ ደግሞ የበለጠ ትኩረትን ይስባል።
ፖለቲካ የወለደው የእግር ኳስ ተቀናቃኝነት ዓመታትን ተሻግሮ ዛሬም የሚሊዮኖችን ቀልብ እንደገዛ ነው።
#ባሕር_ዳር፡ ሐምሌ 9/2018 ዓ.ም
✍️ በመልሰው ጥበቡ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here