“በብሔራዊ ቡድናችን ላይ የአድሎ ወንጀል ተፈጽሟል” የግብፅ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

0
70
የግብፅ እግር ኳስ ማኅበር በአርጀንቲና በነበረባቸው የ16ቱ ክለቦች የዓለም ዋንጫ ሽንፈት ወቅት ጨዋታውን የመሩት ዳኞች ከውድድሩ እንዲባረሩ ፊፋን መጠየቁን አስታውቋል።
ማኅበሩ ለዓለም እግር ኳስ አሥተዳዳር አካል ፊፋ አቤቱታ ማስገባቱን የገለጸ ሲኾን በአትላንታ በተደረገው ጨዋታ ላይ በታየው ዳኝነት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቋል።
የግብፅ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሃኒ አቡ ሪዳ በዳኞች ቡድን በተፈጸሙ ከባድ የስህተት ውሳኔዎች ምክንያት የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታውን እንዲሸነፍ እና ከዓለም ዋንጫው እንዲወጣ በማድረጋቸው በፈረንሳዊው ዳኛ ፍራንሷ ሌቴክሲየር ላይ ምርመራ እንዲደረግ ለፊፋ አቤቱታ አቅርበዋል።
ማኅበሩ “ግልጽ የኾኑ ስህተቶች ተፈጽመዋል፤ እንዲሁም አንዳንድ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ላለመመልከት ድርቅ ብለዋል” በማለት በዋና ዳኞቹ እና በቪዲዮ ቴክኖሎጂ ዳኞች ቡድን ላይ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።
በመግለጫውም “እነዚህን ስህተቶች ከመረመረ በኋላ ዋናው ዳኛ እና መላው የዳኞች ቡድን ከዓለም ዋንጫው እንዲገለሉ” የጠየቀ ሲኾን “በግብፅ ብሔራዊ ቡድን ላይ የአድሎ ወንጀል ተፈጽሟል ሲል መክሰሱን ቢቢሲ አስነብቧል።
በቴዎድሮስ ኃይለኢየሱስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here