ባሕር ዳር: ሰኔ 24/2018 ዓ.ም በዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ቤልጂየም ሴኔጋልን በማሸነፍ ወደ ሚቀጥለው ዙር አልፋለች።
እስከ 86ኛው ደቂቃ ድረስ 2ለ0 የመራችው ሴኔጋል ውጤት ማስጠበቅ ሳትችል ቀርታለች። ቤልጂየም ከ2ለ0 መመራት ተነስታ 3ለ2 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች።
የሴኔጋልን ግቦች ሃቢብ ዲያራ እና እስማኤላ ሳር አስቆጥረዋል። የቤልጂዬምን የማሸነፊ ግቦች ደግሞ ዩሪ ቴልማንስ ሁለት ሲያስቆጥር ሮሜሮ ሉላኮ ደግሞ ቀሪዋን ግብ አስቆጥሯል።
በሌላ ጨዋታ አሜሪካ ቦሲኒያ እና ሄርዜጎቪኒያን 2ለ0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች።
አሚኮ_ዜና #ስፖርት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!።



