ባሕር ዳር: ሰኔ 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ23ኛው የዓለም ዋንጫ የምድብ አምስት እና ምድብ ሰድስት ጨዋታዎች ወደ ቀጣይ ዙር የሚያልፉትን ለይቷል።
ጃፓን እና ስዊድን 1 ለ 1 ፣ ኔዘርላንድስ ቱኒዚያን 3 ለ 1፣ አይቮሪ ኮስት ኩራካዎን 2 ለ 0 እና ኤኳዶር ጀርመንን 2 ለ 1 በኾነ ውጤት አሸንፈዋል።
ይህን ውጤት ተከትሎም አይቮሪ ኮስት ኩራካኦን በማሸነፍ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቀጣዩ የማጣሪያ ጨዋታ ማለፏን አረጋግጣለች። ግቦቹንም ኒኮላስ ፔፔ አስቆጥሯል።
አይቮሪ ኮስት በ6 ነጥብ የምድብ አምስት ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ነው ማለፏን ያረጋገጠችው።
ሌላው ኢኳዶር ጠንካራዋን ጀርመንን ያሸነፈችበት ጨዋታ ሲኾን ውጤቱን ተከትሎ ኢኳዶር ወደ ቀጣዩ 32ቱ የማጣሪያ ጨዋታ ማለፏን አረጋግጣለች።
ኢኳዶር በምድብ አምስት በ4 ነጥብ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ካለፉት ምርጥ 3ኛ ቡድኖች አንዷ በመኾን ለቀጣዩ ዙር አልፋለች። ጀርመን ምንም እንኳ በዚህ ጨዋታ ብትሸነፍም በ6 ነጥብ በግብ ክፍያ ምድቡን በአንደኝነት አጠናቃለች። ይህ ድል ለኢኳዶር በዓለም ዋንጫ ታሪኳ ከ2006 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ጥሎ ማለፍ ያለፈችበት ትልቅ ስኬት ነው።
ኔዘርላንድስ ቱኒዚያን ያሸነፈችበት ጨዋታ ሌላው ክስተት ሲኾን ኔዘርላንድ ቀጣዩን ዙር መቀላቀሏን አረጋግጣለች። አስቀድማ ከውድድሩ ውጭ መኾኗ የተረጋገጠው ቱኒዚያ በዚህ ጨዋታ ድንቅ ብቃቷን አሳይታለች።
በጃፓን እና በስዊድን መካከል የተደረገው ፉክክር 1ለ1 ነው ያለቀው። ይህንን ውጤት ተከትሎም ጃፓን እና ስዊድን አንድ አንድ ነጥብ በማግኘት በምድባቸው ውስጥ ያላቸውን የበላይነት በማረጋገጥ በጋራ ወደ ቀጣዩ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ መሸጋገራቸውን አረጋግጠዋል።
#አሚኮ_ዜና #ስፖርት



