ሪያል ማድሪድ በሴቶች እግር ኳስ ታሪክ ውዱን ዝውውር ፈጸመ !

0
13

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የስፔኑ ታላቅ ክለብ ሪያል ማድሪድ የ19 ዓመቷን ስዊድናዊት የፊት መስመር ተጫዋች ፌሊሺያ ሽሮደርን በታሪክ የሴት ተጫዋቾች ከፍተኛ የዝውውር ሒሳብ ማስፈረሙን ቢቢሲ ስፖርት አስነብቧል።

ሽሮደር ባለፈው የውድድር ዓመት በአውሮፓ መድረክ ያስመዘገበችው ብቃት አስደናቂ እንደነበር ይታወሳል።

ተጫዋቿ ክለቧ ቢኬ ሄከን ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደውን የሴቶች የአውሮፓ ዋንጫ ሲያነሳ የፍጻሜ ጨዋታው ላይ አራቱንም ጎሎች በብቸኝነት በማስቆጠር የዓለምን ትኩረት ስባለች።

ይህን ተከትሎም እንደ ቼልሲ ያሉ የአውሮፓ ኃያላን ሲፈልጓት ቢቆዩም በመጨረሻ ግን ማድሪድን መርጣለች ተብሏል።

የዝውውር ሒሳቡ በይፋ ባይገለጽም ግን ቀደም ሲል ተመዝግቦ ከነበረው የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር የዓለም የምንጊዜውም ውድ የሴቶች ዝውውር ክብረወሰን የላቀ መኾኑ ተረጋግጧል።

በሪያል ማድረግ ቤት ለ4 ዓመት ሚያቆያትን ውል እንደተፈራረመችም ተገልጿል።

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት

በሳሙኤል ጥሩነህ (የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአሚኮ የተግባር ተማሪ)

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here