ባሕር ዳር: ሰኔ 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞው የሪያል ማድሪድ ኮከብ ጋሬዝ ቤል ሆሴ ሞሪንሆ ወደ ሳንቲያጎ በርናባው ስለመመለሳቸው እና በትልልቅ ክለቦች ውስጥ ስለሚኖረው የአሠልጣኝነት ሚና ለታዋቂው ”ዘ አትሌቲክ” ሚዲያ አስተያየት ሰጥቷል።
ቤል በአሁኑ ወቅት በማድሪድ የመልበሻ ክፍል ውስጥ አለመረጋጋት እንዳለ በመጠቆም የሞሪንሆ መምጣት ቡድኑን መስመር ለማስያዝ ወሳኝ መኾኑን ገልጿል።
የመልበሻ ክፍሉ በጥቂቱ የተመሰቃቀለ ይመስላል ያለው ቤል ልምድ ያለው ዋና አሠልጣኝ መምጣቱ፤ ሆሴ ቡድኑን እንደሚያረጋጋው እና ሁሉንም በአንድ መስመር ላይ እንደሚያሰልፋቸው ተስፋ አደርጋለሁ” ሲል የሞሪንሆ ጠንካራ ስብዕና አሁን ላለው ማድሪድ አስፈላጊ መኾኑን አስምሮበታል።
በተጨማሪም ቤል በትልልቅ ክለቦች ውስጥ ስላለው የአሠልጣኝነት ፍልስፍና ሲናገር የካርሎ አንቼሎቲን ስኬት በምሳሌነት አንስቷል።
እንደ ሪያል ማድሪድ ባሉ ትልልቅ ክለቦች ውስጥ በእርግጥ ማሠልጠን አያስፈልግህም ያለው ቤል ማሥተዳደር ያለብህ የተጫዋቾችን ፍላጎት እና ኩራት ነው ብሏል።
ካርሎ አንቼሎቲ በትልልቅ ክለቦች ውስጥ ይህን ያህል ስኬታማ ሊኾን የቻለው ለዚህ ነው በማለት ሀሳቡን አጋርቷል።
#አሚኮ_ዜና #ስፖርት
በሳሙኤል ጥሩነህ (ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአሚኮ የተግባር ተማሪ)
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



