ፖርቹጋል ከ ኡዝቤኪስታን እና እንግሊዝ ከ ጋና ዛሬ ምሽት የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

0
33
ባሕር ዳር: ሰኔ 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ23ኛው የዓለም ዋንጫ የዛሬ መርሐ ግብር ምሽት 2:00 ፖርቹጋል ከ ኡዝቤኪስታን የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
በመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ከዴሞክራቲክ ሪፕብሊክ ኮንጎ ጋር የተገናኙት ፖርቹጋሎች 1 ለ 1 በኾነ ውጤት ማጠናቀቃቸው ይታወሳል።
በ23ኛው የዓለም ዋንጫ ውድድር በተጠበቁት ልክ እንቅስቃሴ ማሳየት ያልቻሉት ፖርቹጋሎች ከአቻ ውጤቱ በኋላ የሚወጡ መረጃዎች የተጫዎቾች የቡድን አንድነት መንፈስ የላላ መኾኑ እየተገለጸ ነው።
የፖርቹጋል ታሪካዊ ተጫዎች ክርስቲያኖ ሮላንዶ ከባለፈው ጭዋታ የተሻለ እንቅስቃሴ ያሳይ ይኾን የሚለው ጉዳይ በእግር ኳስ አፍቃሪያን ዘንድ ዛሬ በጉጉት ይጠበቃል።
ከምድቧ አንድ ነጥብ ይዛ ሦሥተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ፖርቹጋል በ3 ነጥብ ምድቡን እየመራች የምትገኘውን ኮሎምቢያን በልጣ የምድቡ መሪ ለመኾን የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ይጠበቅባታል።
በሌላ የዛሬ መርሐ ግብሮች ምሽት 5:00 እንግሊዝ ከ ጋና የሚገናኙ ሲኾን ሁለቱም የመጀመሪያውን ጨዋታ አሸንፈው በእኩል 3 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ምድቡን እየመሩ ያሉ ቡድኖች ናቸው።
ሁለቱ ቡድኖች የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ለጥሎ ማለፍ ለመድረስ ሁነኛ መንገድ በመኾኑ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።
በሌላ በኩል ሌሊት 8:00 ፓናማ ከ ክሮሺያ እና ንጋት 11:00 ኮሎምቢያ ከ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here