ባሕር ዳር: ሰኔ 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ2026 የዓለም ዋንጫ የተሳታፊዎች ቁጥር ወደ 48 ማደጉን ተከትሎ፣ ከ12ቱ ምድቦች አንደኛ እና ሁለተኛ ከሚወጡት በተጨማሪ 8 ሀገራት ምርጥ ሦሥተኛ ኾነው ወደ 32ቱ ጥሎ ማለፍ የመቀላቀል ዕድል አላቸው።
የኦፕታ የመረጃ ትንተና እንደሚያሳየው ቡድኖች ምርጥ ሦሥተኛ ኾነው ለማለፍ የሚከተሉትን ነጥቦች ማሳካት ይጠበቅባቸዋል።
1ኛ አምስት እና ስድስት ነጥብ ማግኘት ያለምንም ጥርጥር በቀጥታ ማለፍ ያስችላቸዋል።
2ኛ አራት ነጥብ ማግኘት የማለፍ ዕድሉ እጅግ ሰፊ ነው።
3ኛ ሦሥት ጥብ ማግኘት ዝቅተኛው የማለፊያ ነጥብ ነው። በዚህ ደረጃ የግብ ክፍያ ማለትም ንፁሕ ግብ ያላቸው ከግብ ዕዳ ካለባቸው የተሻለ ዕድል ይኖራቸዋል።
ቀደም ሲል 4 ምርጥ ሦሥተኛ ሀገራት ያልፉ ነበር። ዘንድሮ ግን የሀገራት ቁጥር በመጨመሩ የዕድሉ ተጠቃሚዎች ቁጥር ወደ 8 አድጓል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
S



