ባሕር ዳር: ሰኔ 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ክሪስታል ፓላስ ከኦሊቨር ግላስነር ጋር መለያየቱን ተከትሎ የቀድሞውን የሌንስ አሠልጣኝ ፒየር ሴጅን ለሦሥት ዓመታት በሚቆይ ውል በዋና አሠልጣኝነት መሾሙን ይፋ አድርጓል።
እንደ ስካይ ስፖርት ዘገባ የ47 ዓመቱ ፈረንሳዊ አሠልጣኝ ፒየር ሴጅ ባለፈው የውድድር ዘመን ሌንስን በፈረንሳይ ሊግ ሁለተኛ ደረጃ እንዲይዝ ማድረግ የቻሉ ሲኾን በክለቡ ታሪክ የመጀመሪያውን የፈረንሳይ ዋንጫ በማሳካት የሊግ 1 የዓመቱ ምርጥ አሠልጣኝ ኾነው መመረጣቸው ይታወሳል።
#አሚኮ_ዜና #ስፖርት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



