ባሕር ዳር: ሰኔ 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ለስፔን እና ለሪያል ሶሲዳድ የሚጫወተው ሚኬል ኦያርዛባል በዓለም ዋንጫ ታሪክ ውስጥ ማንም ሊይዘው የማይፈልገውን ታሪካዊ ሪኮርድ አስመዝግቧል።
ተጫዋቾች በጨዋታ ላይ የሚያደርጉት የኳስ ንክኪ በይፋ መመዝገብ ከተጀመረበት እ.አ.አ. 1966 ወዲህ በመጀመሪያዎቹ 30 ደቂቃዎች ሜዳ ውስጥ ቢቆይም ኳስን ሳይነካ ወጥቷል በሚል ነው አዲስ ታሪክ ያስመዘገበው።
ክስተቱ የተፈጠረው በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ላይ የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከኬፕ ቨርዴ ጋር ባደረገው የምድብ ጨዋታ ላይ መኾኑን ስካይ ስፖርት አስነብቧል።
በስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



