የቱኒዚያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሠልጣኝ ሳብሪ ላሙቺን አሰናበተ።

0
11

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የቱኒዚያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ ቡድኑ በዓለም ዋንጫ መክፈቻ ጨዋታ በስዊድን 5ለ1 በኾነ ሰፊ ውጤት መሸነፉን ተከትሎ የ54 ዓመቱን ዋና አሠልጣኝ ሳብሪ ላሙቺን ማሰናበቱን ዘ ሰን ዘግቧል። ውሳኔው የተላለፈው የፌዴሬሽኑ አመራሮች ባደረጉት አስቸኳይ ሥብሠባ ሲኾን ደጋፊዎች ግን ውሳኔውን በዓለም ዋንጫ መድረክ ላይ የተወሰደ አስከፊ እርምጃ ሲሉ እየተቹት ይገኛል።

አሠልጣኝ ላሙቺ የካርቴጅ ንስሮቹን መምራት ከጀመሩ በኋላ በሄይቲ ላይ ካስመዘገቡት ብቸኛ ድል ውጭ ካናዳ፣ ኦስትሪያ፣ ቤልጂየም እና ስዊድን ጋር ባደረጓቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም።

ቱኒዚያ የፊታችን ቅዳሜ ከጃፓን ጋር ወሳኝ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዋን የምታደርግ በመኾኑ የቀድሞውን ኮከብ ዋህቢ ኸዝሪን ወይም የቀድሞውን አሠልጣኝ ሞንድሄር ኬባየርን በጊዜያዊነት ለመሾም ማሰቧ ተገልጿል።

#አሚኮ_ዜና # ስፖርት

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here