ባለፉት ሦስት የዓለም ዋንጫዎች ትንበያ ያልተሳሳተው ተንባይ ኔዘርላንድስ የ2026 ዓለም ዋንጫን ታነሳለች አለ።

0
38

 

​ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) እ.አ.አ በ2014 ጀርመንን፤ በ2018 ፈረንሳይን እና በ2022 አርጀንቲና የዓለም ዋንጫን እንደሚያነሱ አስቀድሞ በትክክል የተነበየው ጀርመናዊው የምጣኔ ሀብት እና የስታቲስቲክስ ባለሙያ ዮአኪም ክሌመንት ለ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ኔዘርላንድስ ሻምፒዮን እንደምትኾን አዲስ ትንበያውን ይፋ አድርጓል።

የክሌመንት የትንበያ ሞዴል ከስፖርታዊ መረጃዎች ባሻገር የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና የሥነ-ሕዝብ ስሌቶችን አቀናጅቶ የሚሠራ ነው።

በሰውየው በሂሳብ ቀመሩ መሠረት የሆላንድ ብሔራዊ ቡድን በታላቁ ፍጻሜ ፖርቹጋልን በማሸነፍ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫን ያነሳል።

ይህ ትንበያ እንደ ፈረንሳይ፣ አርጀንቲና፣ ስፔን እና እንግሊዝ ያሉ የቅድሚያ ግምት ያገኙ ኃያላን ሀገራትን ወደ ጎን በመተው ለኔዘርላንድስ ቅድሚያ በመስጠቱ የስፖርት ተንታኞችን ትኩረት ስቧል።

እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን በ1974፣ 1978 እና 2010 ለፍጻሜ ደርሳ በሦሥቱም የተሸነፈችው ኔዘርላንድስ በአሠልጣኝ ሮናልድ ኩማን እየተመራች አዲስ ታሪክ ትሠራ ይኾን የሚለው ከወር በኋላ ምላሽ የሚያገኝ ይኾናል።

ኢ ኤስ ፒ ኤን የዜና ምንጭ ባወጣው መረጃ ባለሙያው እግር ኳስ በማይታሰቡ ክስተቶች እና በዕድል የሚወሰን በመኾኑ ቀመሩ ፍጹም እንዳልኾነ ቢገልጽም ያለፉት ሦሥት ተከታታይ ስኬቶቹ ግን አዲሱን ስሌቱን በስፖርቱ ዓለም በከፍተኛ ጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል።

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት_እግር_ኳስ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here