ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) አርሰናል የባርሴሎና እና የሊቨርፑል ኢላማ የነበረውን የ23 ዓመቱን የአትሌቲክ ክለብ እና የስፔን ብሔራዊ ቡድን ኮከብ ክንፍ ተጫዋች ኒኮ ዊሊያምስን ለማስፈረም አሁንም በጽኑ ፍላጎት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ተጫዋቹን ለማግኘት ሊቨርፑል፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድም ፍላጎት አሳይተዋል ሲል ስካይ ስፖርት አስነብቧል።
እንደ ማርካ ዘገባ የጣሊያኑ ኃያል ክለብ ጁቬንቱስ የአርጀንቲናውን የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝን ከአስቶን ቪላ ለመውሰድ ንግግር ጀምሯል። የ33 ዓመቱ ግብ ጠባቂ ከጁቬንቱስ ጋር በግል ጥቅማጥቅሞች ላይ ቀድሞውኑ ስምምነት ላይ ደርሷል።
የፈረንሳዩ ፒኤስጂ በጀርመኑ ባየር ሙኒክ ቤት ድንቅ ብቃቱን እያሳየ የሚገኘውን የ24 ዓመቱን ፈረንሳዊ አጥቂ ሚካኤል ኦሊሴን በዚህ የክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ፓሪስ ለማምጣት ጥረት ለማድረግ አቅዷል ሲል ዘሰን ዘግቧል።
እንደ ዘጋርዲያን ዘገባ ባርሴሎናዎች ለስፔኑ ኮከብ ዳኒ ኦልሞ ከቼልሲ እና ከአርሰናል በኩል ያለውን ፍላጎት ጠንቅቀው ያውቃሉ። ኾኖም የ28 ዓመቱን አማካይ ለመልቀቅ ክለቡ የያዘው የ60 ሚሊዮን ፓውንድ ዋጋ መሟላት እንዳለበት አቋም ይዘዋል።
ሊቨርፑል ጣሊያናዊውን አጥቂ ፌደሪኮ ኬዛን በዚህ ክረምት በ17 ሚሊዮን ፓውንድ አካባቢ ለመልቀቅ ዝግጁ ነው። ተጫዋቹ ራሱም ወደ ሀገሩ ጣሊያን ሴሪአ የመመለስ ከፍተኛ ፍላጎት አለው ሲል ስካይ ስፖርት በገጹ አጋርቷል።
#አሚኮ_ዜና #ስፖርት_እግር_ኳስ
በምስጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



