ሊቨርፑል አሠልጣኝ አርኔ ስሎትን አሰናበተ።

0
59

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ)ሊቨርፑል አሠልጣኝ አርኔ ስሎትን አሰናብቷል።

ከየርገን ክሎፕ ወርቃማ ዓመታት በኋላ ሊቨርፑልን የተረከቡት አሠልጣኝ አርኔ ስሎት በመጡበት ዓመት የእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ዋንጫን አሸንፈዋል። በሁለተኛው የውድድር ዘመናቸው ግን ሊቨርፑል ተዳክሞ ታይቷል።

በርካታ ተጨዋቾችችን ያሰፈረመው ሊቨርፑል የበለጠ ተጠናክሮ ይቀርባል ሲባል ደካማ የውድድር ዓመትን አሳልፏል። ለሊቨርፑል መድከም ደግሞ ቀዳሚው ተጠያቁ አሠልጣኙ መኾናቸው ሲገለጽ ቆይቷል።

ሊቨርፑልም የክለቡን ጥንካሬ ዳግም ለመመለስ አሠልጣኙን ማሰናበቱን ዘ ሰን ስፖርት ዘግቧል። አሠልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ ሊቨርፑልን የሚረከቡት ቀዳሚው ምርጫ መኾናቸውን ፋብሪዚዮ ሮማኖ ጽፏል።

ክለቡ ሊቨርፑልም በድረ ገጹ በጋራው መረጃ አርኔ ስሎት ከዋና አሠልጣኝነት ሚናቸው መልቀቃቸውን አስታውቋል። እሳቸውን የሚተካ አሠልጣኝ የመቅጠር ሂደት መጀመሩን ገልጿል።

​አንድ የፕሪምዬር ሊግ ዋንጫ ላሸነፉት አሠልጣኙ ምስጋና እና አድናቆት እንዳለውም አስታውቋል።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here