አሠልጣኝ ሚኬል አርቴታ የዓመቱ ምርጥ አሠልጣኝ ኾነው ተመረጡ።

0
31

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) አርሰናል የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ማሸነፉን ተከትሎ አሠልጣኝ ሚኬል አርቴታ የዓመቱ ምርጥ አሠልጣኝ ኾነው ተመርጠዋል።

አርሰናልን ለሊጉ ዋንጫ ያበቁት ሚኬል አርቴታ የሊጉን ተቀናቃኝ ማንቸስተር ሲቲን በ7 ነጥብ ልዩነት በመብለጥ የ2025/26 የውድድር ዘመን የፕሪምየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ ኾነዋል።

ይህ ድል አርሰናል ከ22 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ያነሳው የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ነው። አርቴታ ቡድኑን እንደፈረንጆቹ ዘመን በታኅሣሥ 2019 በዝቅተኛ ደረጃ ላይ እያለ ከተረከቡ በኋላ ባሉት 6 ዓመታት ውስጥ ጠንካራ ተፎካካሪ አድርገው መገንባት ችለዋል።

ፍላሽ ስኮር እንደዘገበው አርቴታ ለሽልማቱ ያበቃቸው ቡድኖቻቸውን ወደ አውሮፓ መድረክ ማሳለፍ የቻሉትን የቦርንማውዙን አንዶኒ ኢራኦላን እና የሰንደርላንዱን ሬጂስ ሌ ብሪስን በመብለጥ ነው።

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት #የእንግሊዝ_ፕሪምየርሊግ

በምስጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here