በእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

0
22

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ የ2025/26 የውድድር ዓመት ማጠናቀቂያ ላይ በደረሰበት በዚህ ወቅት የሊጉን ዋንጫ ለማሸነፍ የሚደረገው ፉክክር ከፍ ብሏል።

የሊጉ መሪ አርሰናል ትናንት ወሳኝ ድል አስመዝግቧል። የሊጉ ተከታይ ማንቸስተር ሲቲ ደግሞ እስከመጨረሻው ጨዋታ ድረስ ለዋንጫ ለመፎካከር ዛሬ ከቦርንማውዝ ጋር ይጫወታል።

በቦርንማውዝ ሜዳ ቪታሊቲ ስታዲየም የሚካሄደው ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል። ጨዋታው ምሽት 3፡30 ይካሄዳል።

ከአርሰናል በአምስት ነጥቦች ርቆ የሚገኘው ማንቸስተር ሲቲ በዋንጫ ፉክክር ለመቆየት የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ግድ ይለዋል። ዛሬ ማንቸስተር ሲቲ ከተሸነፈ ወይም ነጥብ ከተጋራ አርሰናል አንድ ጨዋታ እየቀረው ዋንጫውን ማሸነፉን ያረጋግጣል።

ጠንካራ የውድድር ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው
ቦርንማውዝ ለማንቸስተር ሲቲ ፈተና እንደሚኾንበት ይጠበቃል። ቦርንማውዝ ላለፉት 16 ጨዋታዎች አልተሸነፈም፤ ለዛሬው ጨዋታም ጠንካራ ተፎካካሪ እንደሚኾን ይጠበቃል።

የአውሮፓ ውድድር ተሳትፎን ለማረጋገጥ እየተጫወተ የሚገኘው ቦርንማውዝ በ55 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በእርስ በእርስ ግንኑነት ማንቸስተር ሲቲ የበላይነት አለው፤ የዛሬው ጨዋታ ግን ከእስካሁኖቹ እንደሚለይ ይጠበቃል።

ላለመውረድ የሚጫወተው ቶተንሃም ሆትስፐርስ በለንደን ደርቢ ከቸልሲ ጋር ይጫወታል። ቶተንሃም የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ወይም አቻ መውጣት በሊጉ እንዲቆይ ያደርገዋል። ጨዋታው በቼልሲ ሜዳ ስታንፎርድ ብሪጅ ምሽት 4:15 ይካሄዳል።

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት#

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here