ዘ ስፔሻል ዋን ጆዜ ሞሪኒሆ የሪያል ማድሪድ አሠልጣኝ ለመኾን ተስማሙ።

0
37

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፖርቹጋሉን የእግር ኳስ ቡድን በማሠልጠን ላይ የነበሩት የእግር ኳስ አሠልጣኙ ጆዜ ሞሪኒሆ ባለፉት ጊዜያት ቤኔፊካ ያቀረበላቸውን የኮንትራት ማራዘም ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው ይታወሳል።

አሠልጣኙ አሁን ላይ በውጤት ማጣት እና በከፍተኛ ቀውስ ውስጥ የሚገኘውን ሪያል ማድሪድን ለማሠልጠን ከቃል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ፋብሪዚዮ ሮማኒዮ አረጋግጧል።

ክለቡ ለተከታታይ ሁለት የውድድር ዓመታት ትልልቅ ዋንጫዎችን ባለማሳካቱ እና በክለቡ ውስጥ የተፈጠረውን የተጫዋቾች አለመስማማት ተከትሎ የክለቡ ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ የቡድኑን መንፈስ መስመር ለማስያዝ ሞሪኒሆን ቀዳሚ ምርጫቸው አድርገዋል ተብሏል።

ጆዜ ሞሪኒሆ ከዚህ ቀደም እ.አ.አ ከ2010 እስከ 2013 ባሉት ዓመታት ሪያል ማድሪድን ማሠልጠናቸው እና በ2011/12 በአስገራሚ የነጥብ እና የግብ ክብረ ወሰን የላሊጋውን ዋንጫ ማንሳታቸው ይታወሳል።

ከ13 ዓመታት በኋላ ወደ ሎስብላንኮቹ ቤት የተመለሱት ዘ ስፔሻል ዋን ጆዜ ሞሪኒሆ እስከ 2028 የሚያቆያቸውን የውል ስምምነት ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ ፦ አድኖ ማርቆስ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here