ኢትዮጵያ ከሞሮኮ ጋር ዛሬ ትጫዎታለች።

0
14

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ሁለተኛውን የምድብ ጨዋታ ከሞሮኮ አቻው ጋር ያደርጋል።

ዛሬ በአሠልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሞሮኮን አሸንፎ ለመውጣት ብርቱ ፉክክር ያደርጋል።

ብሔራዊ ቡድኑ ለዚህ ወሳኝ ውድድር ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየ መኾኑን የኢትዮጵያ ፉት ቦል ፌዴሬሽን በማኅበራዊ ገጹ አስፍሯል።

ተጫዋቾቹም ምሽት 2፡00 ላይ ለሚካሄደው ጨዋታ ውጤታማ ለመኾን ዝግጁ መኾናቸው ተመላክቷል።

በዘንድሮው የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ላይ 16 የአሕጉሪቱ ሀገራት የሚሳተፉ ሲኾን በውድድሩ ጥሩ ውጤት የሚያስመዘግቡ 10 ሀገራት በኳታር አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ የማለፍ ዕድል የሚያገኙ ይኾናል።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here