በ19ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ወደ ግላስጎው አቀና።

0
263

ባሕር ዳር: የካቲት 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚካፈለው የኢትዮጵያ ልዑክ ወደ ግላስጎው አቅንቷል፡፡

19ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከፈረንጆቹ መጋቢት 1 እስከ 3 ቀን 2024 በግላስጎው እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡

ኢትዮጵያን ወክሎ በውድድሩ ለሚካፈለው የልዑካን ቡድንም ዛሬ ዕኩለ ቀን ላይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሽኝት ተደርጎለታል፡፡

በሽኝት ሥነ-ሥርዓቱም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ሌሎችም አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here