ባሕር ዳር: ግንቦት 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሲቪኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 32ኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ ሲቀጥል ሦሥት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
በ31ኛ ሳምንት የደረጃ ሠንጠረዥ ላይ በ41 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ባሕር ዳር ከተማ በ34 ነጥብ 17ኛ ጀረጃ ላይ ከሚገኘው ደሬዳዋ ከተማ ጋር ነው የሚጫወተው።
ባሕር ዳር ከተማ ባለፈው የሊጉ ሳምንት ጨዋታ ላይ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ተገናኝቶ ያለግብ ነው ነጥብ የተጋራው። ዛሬ ቡድኑ ሦሥት ነጥቡን ለማሳካት ይጫወታል።
የዛሬ ተጋጣሚው ደሬዳዋ ከተማ በነገሌ አርሲ 3ለ0 የተሸነፈ ቡድን ነው። ጨዋታውም በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ቀን 10:00 ላይ ይካሄዳል።
በሌላ የሊጉ ጨዋታ መቀለ 70 እንደርታ ከኢትዮጵያ መድን ቀን 7፡00 ላይ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሸገር ከተማ ጋር 10፡00 ላይ በተመሳሳይ በአዲስ አበባ አበበ ቢቄላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
