ባሕርዳር፡ ግንቦት 05/2018ዓ.ም (አሚኮ) ማንቸስተር ዩናይትድ እና ጊዜአዊ አሠልጣኙ ማይክል ካሪክ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን እና ከዚያም በላይ አብረው ለመቀጠል መስማማታቸውን ቢቢሲ በድረገጹ አስፍሯል።
ለሳምንታት ሲዘገብ እንደቆየው ሁሉ የማንቸስተር ዩናይትድ እና ማይክል ካሪክ ጥምረት የመቀጠል ዕድሉ እየሰፋ የመጣ ሲኾን በክለቡ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው እርሱ መቆየት አለበት የሚል ዕምነት አለው ነው የተባለው።
ተጫዋቾች፣ መሪዎች እና ሁሉም አካል በአንድ ሃሳብ ላይ ተስማምተዋል።
ቀጣዩ ደረጃ ንግግሮችን ወደ መጨረሻው ምዕራፍ በማድረስ አዲሱን ስምምነት መፈረም ይኾናል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !



