ማንቸስተር ሲቲ ለዋንጫ ያለውን ተስፋ ከፍ የሚያደርግበት ጨዋታ !

0
31
ባሕር ዳር: ግንቦት 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ማንቸስተር ሲቲ ከክሪስታል ፓላስ የሚያደርጉት ጨዋታ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል።
ይህ ጨዋታ የዋንጫውን መዳረሻ ምንአልባትም በግልጽ የሚጠቁምበት ሁኔታ ሊፈጠር ስለሚችል በጉጉት ይጠበቃል።
ማንቸስተር ሲቲ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በክሪስታል ፓላስ ላይ ግልጽ የኾነ የበላይነት ያለው ቢኾንም ፓላሶች ግን በኢቲሀድ ስታዲየም ባደረጓቸው ያለፉት ጨዋታዎች በሲቲ መረብ ላይ ተደጋጋሚ ግቦችን የማስቆጠር ብቃት አሳይተዋል።
ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ላይ ያለመሸነፍ ጥንካሬውን አስቀጥሏል። በአንጻሩ ክሪስታል ፓላስ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በሜዳው ከሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ይልቅ ከሜዳው ውጭ ባለው ውጤታማነት የሚጠቀስ ሲኾን ይህም ለሲቲ ተከላካዮች ስጋት ሊኾን እንደሚችል ይገመታል።
የማንቸስተር ሲቲው ግብ አዳኝ ኧርሊንግ ሀላንድ በፓላስ ላይ ግብ የማስቆጠር ልማዱን ለማስቀጠል ሲጠበቅ ዶኩም በቅርብ ጊዜያት እያሳየ ያለው ድንቅ እንቅስቃሴ ለቡድኑ ትልቅ ጥንካሬ ኾኗል።
በክሪስታል ፓላስ በኩል ደግሞ ዦን ፊሊፕ ማቴታ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ለመክፈት ሲዘጋጅ ኢስማኢላ ሳር በያዘው ግሩም ወቅታዊ አቋም የሲቲን ተከላካዮች ለመፈተን ዝግጁ ኾኖ የጨዋታውን መጀመር ብቻ ይጠብቃል። ጨዋታው ምሽት 4:00 ላይ ይካሄዳል።
በምስጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here