አጓጊው ፍልሚያ በለንደን ደርቢ !

0
66

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ መዳረሻን ለመገመት የሚያስችለው 36ኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ በአርሰናል እና በዌስትሀም ዩናይትድ መካከል ይከናወናል።

የዋንጫ ተፎካካሪው ማንቸስተር ሲቲ ትናንት ብሬንትፎርድን 3ለ0 ማሸነፉን ተከትሎም የዛሬው የለንደን ደርቢ ይበልጥ አጓጊ ኾኖ እንድጠበቅ አድርጎታል።

ሊጉን በ76 ነጥብ እየመራ የሚገኘው አርሰናል የዋንጫ ጉዞውን ትክክለኛ መዳረሻ ፍንጭ ሊሰጥ የሚችለውን ወሳኝ ምዕራፍ በቀላል አሳልፎ የማይሰጥ መኾኑ፤ ቢታመንም የቀጣይ ዓመት የፕሪምየር ሊግ ቆይታውን የሚያሳምርበት ትልቅ ዕድል ነውና ዌስትሃምም አንገት ላንገት መተናነቁ አይቀሬ ይመስላል።

እናም የዛሬው ጫዋታ ሁሌም በየሳምንቱ ከሚደረጉ ጨዋታዎች በተለየ ሁኔታ ለሁለቱም ክለቦች ተጨማሪ ትርጉም ያለው ነው።

መድፈኞቹ ከ22 ዓመታት በኋላ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለመሳም፤ ዌስትሃም ዩናይትድ ደግሞ በሊጉ ለመቆየት የሚያደረግ ፍልሚያ ነው።

ጨዋታው ምሽት 12:30 ላይ የሚካሄድ ሲኾን በአርሰናል በኩል ካይ ሃቨርትዝ እና ማርቲን ኦዴጋርድ ዝግጁ መኾናቸውን አሠልጣኛቸው ሚኬል አርቴታ ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ ስፖርት በድረ ገጹ አስነብቧል። ቲምበር ግን ዛሬም ከጉዳቱ እንደማይመለስ ተገልጿል።

አሠልጣኝ ሚኬል አርቴታ የዛሬውን ጨዋታ ቀላል ትርጉም ሰጥተን የምናየው አይኾንም ሲሉ ተደምጠዋል። ተገቢ የኾነ ዝግጅት ማድረጋቸውንም በልበ ሙሉነት አንስተዋል።

የዌስትሃም ዩናይትዱ አሠልጣኝ ኑኖ እስፒሪቶ ሳንቶ ጨዋታው ለኛ የሞት ሽረት ጉዳይ ነው ብለዋል። በድል ለመወጣትም አልመን እንጫወታለን ነው ያሉት።

በዛሬ የሊጉ መርሐ ግብር ሌሎች ጨዋታዎችም የሚካሄዱ ሲኾን፦

👉 በርኒሌይ ከአስቶንቪላ፦
👉 ክሪስታል ፓላስ ከኤቨርተን፦
👉 ኖቲንግሃም ፎረስት ከኒውካስትል ዩናይትድ ቀን 10:00 ላይ የሚካሄዱ ጨዋታዎች ናቸው።

በሰለሞን አንዳርጌ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here