ተጠባቂው ጨዋታ በአንፊልድ

0
73

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 36ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ሲካሄድ አምስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ከሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታዎች መካከል የኾነው የሊቨርፑል እና የቸልሲ ፉክክር ዛሬ ተጠባቂ ነው። በሊጉ 58 ነጥቦችን በመሠብሠብ አራተኛ ደረጃ የሚገኘው ሊቨርፑል በጥሩ አቋም ላይ ከማይገኘው ቸልሲ ጋር በአንፊልድ ስታድየም የሚያደርጉት ፍልሚያ የሚጠበቅ ነው።

ቸልሲ 48 ነጥብ በመሠብሠብ በሊጉ የደረጃ ሠንጠረዥ ዘጠነኛ ላይ ይገኛል። ሁለቱም ቡድኖች የቀጣይ ዓመት የአውሮፖ ሻምፒዮንስ ሊግ መድረክ ተሳታፊ ለመኾን ስለሚጫወቱ ውድድሩ በቀላል የሚታይ አይኾንም።

ሊቨርፑል ከተከታታይ ሦሥት ጨዋታዎች ድል በኋላ በማንቸስተር ዩናይትድ ሽንፈትን መቅመሱ የሚታወስ ሲኾን ቸልሲ ደግሞ ባለፉት ስድስት ተከታታይ ሳምንታት የቁልቁለት ጉዞ ላይ ነው የቆየው።

እናም በአቋም ደረጃ እርስ በእርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ውስጥ ሊቨርፑል ሦሥቱን ሲያሸንፍ ቸልሲ ደግሞ በሁለቱ ድል አድርጓል። ይሁን እና ከወቅታዊ አቋም አንጻር ድል ለሊቨርፑል ልታደላ ትችላለች የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ። ትክክለኛው ምላሽ ግን ቀን 8:30 ላይ የሚደረገው ፍልሚያ እውነቱን የሚያስመለክተን ይኾናል።

በሌላ የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታ ቀን 11:00 ላይ ማንቸስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጭ በመጓዝ ከሰንደርላንድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታም ይጠበቃል። በጥሩ ብቃት ላይ በመገኘት የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊነቱን ያረጋገጠው ማንቸስተር ዩናይትድ ዛሬም ድሉን በሌላ ሜዳ ላይ ብቃቱን ያረጋግጥ ይኾን ?

ከምሽቱ 1:30 ላይ የሚካሄደው ሌላው የዛሬ መርሐ ግብር ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ኢትሃድ ስታድየም ብሬንትፎረድን የሚጋብዝበት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል። ለምን ቢባል የፕሪምየር ሊጉ ዋንጫ አሁንም ወደ ማንቸስተር ሲቲ የሚገባበት ዕድል ያለ በመኾኑ ነው። ማንቸስተር ሲቲ የዛሬውን ግጥሚያ በድል የሚወጣ ከኾነ አርሰናል ጨዋታውን እስከሚያካሂድ ልዩነቱን ወደ ሁለት ነጥብ የሚያጠብ ይኾናል።

በሌሎች የዛሬ የፕሪምየር ሊጉ መርሐ ግብሮች

ፉልሃም ከቦርንማውዝ ቀን 11:00 ላይ፦

ብራይተን ከወልቭስ ቀን 11:00 ላይ የሚካሄዱ ጨዋታዎች መኾናቸውን ቢቢሲ ስፖርት በድረ ገጹ አስነብቧል

በሰለሞን አንዳርጌ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here