ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ)የእንግሊዝ ክለቦች በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ፤ በዩሮፓ ሊግ እና በዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ለፍጻሜ ደርሰዋል።
ትናንት ምሽት በተካሄዱ የዩሮፓ ሊግ እና የዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ለፍጻሜ የደረሱ ክለቦች ታውቀዋል። ሁለቱ የእንግሊዝ ክለቦች የተገናኙበት የዩሮፓ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ አስቶንቪላ ቪላ ኖቲንግሃም ፎረስትን በደርሶ መልስ በማሸነፍ ለፍጻሜ አልፏል።
በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በኖቲንግሃም ፎረስት 1ለ0 ተሸንፎ የነበረው አስቶንቪላ የመልሱን ጨዋታ 4ለ0 አሸንፏል። በድምር ውጤትም 4ለ1 አሸንፎ ለፍጻሜ ደርሷል።
በአሠልጣኝነት ዘመናቸው አራት የዪሮፓ ሊግ ዋንጫዎችም ያሸነፉት የአስቶን ቪላው አሠልጣኝ ኡናይ እምሬ ከአስቶንቪላ ጋር ዋንጫ ካሳኩ የዋንጫ ክብራቸውን ወደ አምስት ከፍ ያደርጋሉ። አስቶንቪላ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ያሸንፋል ተብሎ ቅድመ ግምት ተሰጥቷል።
በሌላ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ፍራይበርግ ስፖርቲንግ ብራጋን በማሸነፍ ለፍጻሜ አልፏል።
የዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚዎችም ተለይተዋል። የአንግሊዙ ክርስቲያል ፓላስ የዩክሬኑን ሻክታር ዶኔትስክ በማሸነፍ ለፍጻሜ ደርሷል።
ክርስቲያል ፓላስ በደርሶ መልስ ውጤት 5ለ2 አሸንፎ ነው ለፍጻሜ የደረሰው። ፓላስ ለፍጻሜ መድረሱን ተከትሎ የእንግሊዝ ክለቦች በሦሥቱም የአውሮፓ ታላላቅ ውድድሮች ለፍጻሜ ይፋለማሉ።
አርሰናል በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ፤ አስቶንቪላ በዩሮፓ ሊግ፣ ክርስቲያል ፓላስ ደግሞ በኮንፈረንስ ሊግ ለፍጻሜ ደርሰዋልና። ለፍጻሜ የደረሱበት የእንግሊዝ ክለቦች ዋንጫውን ካሳኩ ለእንግሊዝ እግር ኳስ ተጨማሪ ስኬት ነው።
በሌላ ጨዋታ የስፔኑ ራዮ ቫልካኖ የፈረንሣዩ
ስትራስቡርግን በማሸነፍ ለፍጻሜ ደርሷል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !



