የዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ።

0
44

 

ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የዩሮፓ ኮንፈረስ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚዎች ዛሬ ይለያሉ።

በአውሮፓ እግር ኳስ አህጉራዊ ውድድሮች ሦሥተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይካሄዳል።

ዛሬ ከሚካሄዱ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታዎች መካከል የአንግሊዙ ክርስቲያል ፓላስ ከዩክሬኑ ሻክታር ዶኔትስክ የሚያደርጉት ጨዋታ አንደኛው ነው።

በመጀመሪያ ጨዋታ ከሜዳው ውጭ 3ለ1 አሸንፎ የተመለሰው ክርስቲያል ፓላስ ወደ ፍጻሜ ለማለፍ ሰፊ ዕድል አለው። ጨዋታው ምሽት 4:00 ላይ ይካሄዳል።

ክርስቲያል ፓላስ ለፍጻሜ የሚደርስ ከኾነ የእንግሊዝ ክለቦች በሁሉም የአውሮፓ ውድድሮች ለፍጻሜ ይደርሳሉ።

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አርሰናል ለፍጻሜ ደርሷል፤ በዩሮፓ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ሁለቱን የእንግሊዝ ክለቦች አስቶንቪላን እና ኖቲንግሃም ፎረስትን አገናኝቷል። አንደኛው ለፍጻሜ ይደርሳል። ሁሉም አህጉራዊ ዋንጫዎች ወደ እንግሊዝ የሚሄዱ ከኾነ ደግሞ ለእንግሊዝ እግር ኳስ ተጨማሪ ክብር እና ታሪክ ነው።

በሌላ ጨዋታ የፈረንሳዩ ስትራስቡርግ እና የስፔኑ ራዮ ቫልካኖ ለፍጻሜ ለመድረስ ይጫወታሉ። የመጀመሪያውን ጨዋታ ራዮ ቫልካኖ 1ለ0 ማሸነፉ ይታወሳል።

ለፍጻሜ ለመድረስ የሚደረገው ፉክክርም ይጠበቃል። ጨዋታው ምሽት 4:00 ላይ ይካሄዳል።

በታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here