ፋሲል ከነማ ከነገሌ አርሲ ዛሬ ጨዋታውን ያደርጋል።

0
47
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 29ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ዛሬም ሲቀጥል በአዲስ አበባ እና በአዳማ ከተማዎች አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ከእነዚህ ጨዋታዎች መካከል ደግሞ 9፡00 ላይ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ስታዲየም ነገሌ አርሲ ከፋሲል ከነማ የሚያደርጉት ጨዋታ ይገኝበታል።
ፋሲል ከነማ በሊጉ የደረጃ ሠንጠረዥ ላይ በ42 ነጥብ እና በ1 የጎል ክፍያ በስድስተኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው።
ነገሌ አርሲ በበኩሉ በ44 ነጥብ እና በ7 የጎል ክፍያ ሦሥተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ይህም ጨዋታው አንዱ ሌላኛውን አሸንፎ ክብሩን ለማስጠበቅ የሚያደርጉት ጨዋታ በመኾኑ ብርቱ ፉክክር እንደሚኖረው ይጠበቃል።
ባለፈው የ28ኛ ሳምንት ጨዋታ በመቀሌ 70 እንደርታ 3ለ0 የተሸነፈው ፋሲል ዛሬ ወደ ማሸነፍ ለመምጣት ነው የሚጫዎተው።
ተጋጣሚው ነገሌ አርሲ በበኩሉ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር በነበረው ያለፈው የሊግ ጨዋታ 1ለ1 ተለያይቶ እና ነጥብ ተጋርቶ ነው የወጣው። የሁለቱ ቡድኖች ወቅታዊ አቋም ሲታይ ተቀራራቢ የሚባል በመኾኑ የተሻለ ጨዋታ እንደሚኖር ይጠበቃል።
በሊጉ መርሐ ግብር መሠረት ሌሎች ጨዋታዎችም ሲካሄዱ ሀድያ ሆሳዕና ከመቀለ 70 አንደርታ 7:00 ላይ፤ አርባምንጭ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 10፡00 ላይ በአዲስ አበባ አበበ ቢቄላ ስታዲየም እና ኢትዮጵያ ቡና ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 12፡00 ላይ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በምስጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here