አትሌት ትግስት አሰፋ የለንደን ማራቶን አሸነፈች።

0
68

 

ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በለንደን ማራቶን አትሌት ትግስት አሰፋ በበላይነት ስታጠናቅቅ የገባችበት ሰዓት በሴቶች ብቻ በራሷ ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረወሰን አሻሽላለች።

በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ ባለው ማራቶን ትግስት አሰፋ እስከ መጨረሻው እልህ አስጨራሽ ፉክክር በማድረግ የገባችበት 2 ሰዓት 15.41 ደቂቃ አዲስ ክብረ ወሰን ሆኖም ተመዝግቧል።

ኬንያውያኑ አትሌቶች ሄለን ኦቢሪ እና ጆይስሊን ጅፕኮስጊ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here