ተጠባቂው የቼልሲ እና የማንቸስተር ሲቲ ጨዋታ።

0
89

 

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 32ኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ ምሽት 12፡30 ላይ ቼልሲ ማንቸስተር ሲቲን በስታምፎርድ ብሪጅ ያስተናግዳል።

ሁለቱ ክለቦች በሊጉ ለ59ኛ ጊዜ የሚገናኙ ሲኾን በቁጥሮች መረጃ መሠረት ቼልሲ 27 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነት ቢኖረውም በሊጉ ሲቲን ለመጨረሻ ጊዜ ያሸነፈው እ.አ.አ በ2021 ነው።

ለቼልሲ ማሸነፍ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ፉክክር ውስጥ ለመቆየት ወሳኝ ሲኾን ማንችስተር ሲቲ ደግሞ ትናንት በአርሰናል መሸነፍ ምክንያት የነጥብ ልዩነቱን ወደ ስድስት ለማጥበብ እና ለዋንጫው ለመቅረብ የዛሬው ድል የግድ ያስፈልገዋል።
በሌሎች መርሐ ግብሮች አስቶንቪላ ኖቲንግሃም ፎረስትን፤ ሰንደርላንድ ደግሞ ወራጅ ቀጣና ውስጥ ከሚገኘው እና በአዲሱ አሠልጣኝ ሮቤርቶ ዴ ዘርቢ ከሚመራው ቶተንሃም ጋር ይጫወታሉ።

ክሪስታል ፓላስ ከኒውካስትል ዩናይትድ የሚያደርጉት ጨዋታም ከሳምንቱ መርሐ ግብሮች አካል ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here