ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ የ26ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም ይቀጥላሉ። ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
ከእነዚህ ጨዋታዎች መካከል ፋሲል ከነማን ከሀዋሳ ከተማ የሚያገናኘው ጨዋታ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀን 9፡00 ላይ ይካሄዳል።
የዛሬው ጨዋታ ብርቱ ፉክክር እንደሚደረግበት ይጠበቃል።
በሌሎች የሊጉ ጨዋታዎች ነገሌ አርሲ ከኢትዮጵያ መድን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ቀን 7፡00 ላይ ይጫወታሉ። አርባምንጭ ከተማ ከሀድያ ሆሳዕና በአበበ ቢቂላ
ስታዲየም ቀን 10:00 ላይ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከወላይታ ዲቻ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ምሽት 12፡00 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



