የኢትዮጵያ ግሎባል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ተመሠረተ።

0
6

 

አዲስ አበባ: መጋቢት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ‎‎የኢትዮጵያ ግሎባል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን መሥራች ጠቅላላ ጉባኤውን በሀረር ከተማ አካሂዷል።

ፌዴሬሽኑ ዕውቅና ከማግኘቱ አስቀድሞ ለስድስት ዓመታት ከክልሎች እና ከተማ አሥተዳደሮች ጋር ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።

ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በክልሎች የማደራጀት እና ሥልጠናዎችን የመስጠት ሥራዎችን አከናውኗል።

ከባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር ዕውቅና ካገኘ በኋላ ጠቅላላ የመሥራች ጉባኤውን ሀረር ከተማ ላይ በማድረግ ተመሥርቷል።

በምሥረታ ጉባኤው ፌዴሬሽኑ ዕውቅና ከማግኘቱ አስቀድሞ በአደራጅ ኮሚቴው የተከናዎኑ ሥራዎች ሪፖርት ክንውንን አቅርቧል።

የአሠልጣኝ እና የዳኝነት ሥልጠናዎችን ጨምሮ በክልሎች እና ከተማ አሥተዳደሮች ስፖርቱን የማስተዋወቅ እና የማስፋፋት ሥራ መሠራቱ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በመድረኩ መተዳደሪያ ደንቡ ላይ ውይይት ተደርጎ በጠቅላላ ጉባኤው ፀድቋል።

የኢትዮጵያ ግሎባል ቴኳንዶ ፌዴሬሽንን ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት የሚመራ ኘሬዝዳንት እና የሥራ አሥፈፃሚ አባላት ተመርጠዋል።

ዘጋቢ፦ ኃይሉ አዳነ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here