ደሴ ከተማ የምድብ “ለ” መሪ ለመኾን ይጫወታል።

0
9
ባሕር ዳር: መጋቢት 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ክፍተኛ ሊግ 18ኛ ሳምንት ዛሬ ሦሥት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። ከእነዚህ ጨዋታዎች መካከል ደሴ ከተማ ከቢሾፍቱ ከተማ እና የሊጉ መሪ ሀላባ ከተማ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡
በቅርብ ርቀት በሊጉ ምድብ “ለ” አንደኛ እና ሁለተኛ ኹነው እየተከታተሉ ያሉት ሀላባ ከተማ እና ደሴ ከተማ ዛሬ ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ የሚመዘገበው ውጤቱ በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ ወሳኝ ተጽዕኖ አለው።
ደሴ ከተማ ባለፈው 17ኛ ሳምንት ጨዋታ ከነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የነበረውን ጨዋታ ሲመራ ቆይቶ በመጨረሻ 1ለ1 በኾነ ውጤት ነጥብ ተጋርቶ መውጣቱ የሊጉን ምድብ የመምራት ዕድል አባክኗል፡፡
ዛሬ ደግሞ በ29 ነጥብ እና በ18 የጎል ክፍያ ሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ደሴ ከተማ በሊጉ ምድብ “ለ” በ31 ነጥብ እና በ10 የጎል ክፍያ አንደኛ ደረጃ ያለውን ሀላባ ከተማ ክለቡ እስኪጫዎትም ቢኾን ለተወሰነ ጊዜ የአንደኛ ደረጃውን ለመረከብ ደሴዎቹ ዛሬ ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ተጋጣሚው ቢሾፍቱ ከተማ 17ኛው ሳምንት ጨዋታ ላይ ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጋር ተገናኝቶ 4ለ1 አሸንፏል። ጨዋታውም 7፡30 ይካሄዳል፡፡
በሌሎች የሊጉ የምድብ “ለ” ጨዋታ አዲስ አበባ ከተማ ከመንጌ ቤንሻንጉል 4፡00፣ የምድብ “ለ” መሪ ሀላባ ከተማ ከ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 10፡00 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here