ባሕር ዳር: መጋቢት 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ)በዓለም አትሌቲክስ የነሐስ ደረጃ በተሰጠው የባርሴሎና ማራቶን አትሌት ፎቴን ተስፋይ በመጀመሪያ የማራቶን ውድድሯ በታሪክ ሁለተኛውን የዓለም ፈጣን ሰአት በማስመዝገብ አሸንፋለች።
አትሌት ፎቴን ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት 10 ደቂቃ 53 ሴኮንድ ወስዶባታል። አትሌት ፎቴን የቦታውን ክብረወሰን በመስበር ነው ማሸነፍ የቻለችው ።
በውድድሩ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አትሌት ዘይነባ ይመር ሦሥተኛ ፣አትሌት ጫልቱ ጬምዴሳ አራተኛ እና አትሌት ያልጋነሽ እስከመች አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን ማጠናቀቃቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



