ትናንት ምሽት የተካሄዱ የኤፍኤ ካፕ ጨዋታ ውጤቶች

0
133

 

ባሕር ዳር: የካቲት 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ አምስተኛ ዙር ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ እና ቸልሲ ተጋጣሚወቻቸውን በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል።

ተጠባቂው የማንቸስተር ሲቲ እና የኒውካስትል ጨዋታ በማንቸስተር ሲቲ አሸናፊነት ተጠናቅቋል። ማንቸስተር ሲቲ ኒውካስትልን 3ለ1 በኾነ ውጤት ነው ያሸነፈው።

በሌላ ጨዋታ ቸልሲ እና ሬክስሀም ያደረጉት ጨዋታ በቸልሲ አሸናፊነት ተጠናቅቋል። የመደበኛ ሰአት 2ለ2 ተጠናቅቆ በተሰጠው ተጨማሪ 30 ዲቀቃ ነው ቸልሲ ሁለት ተጨማሪ ግቦችን አስቆጥሮ 4ለ2 ያሸነፈው።

የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታዎች ዛሬ ሲቀጥሉ ፉልሃም እና ሳውዝአምፕተን ቀን 9:00 ይጫወታሉ። ፖርት ቫሊ ከሰንደርላንድ 10:30 ሲጫወቱ ሊዲስ ዩናይትድ ከኖሪዊች ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ደግሞ ምሽት 1:30 ይካሄዳል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here