ሪያል ማድሪድ ያልተጠበቀ ሽንፈት አጋጠመው።

0
47

 

ባሕር ዳር፡ የካቲት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በስፔን ላሊጋ ሪያል ማድሪድ በጌታፊ ተሸንፏል።

ሪያል ማድሪድ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት 1ለ0 ነው የተሸነፈው።

የጌታፌን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ማርቲን ሳትሪያኖ በ39ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።

በጨዋታ ማብቂያዎቹ ደቂቃዎች የማድሪዱ ፍራንኮ ማስታንቱኖ በቀይ ካርድ እና የጌታፌው አድሪያን ሊሶ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ ወጥተዋል።

የሪያል ማድሪድ በዚህ ጨዋታ ሦሥት ነጥብ ማጣት ከመሪው ባርሴሎና ጋር ያለውን ልዩነት ወደ አራት ከፍ አድርጎታል።

ላሊጋውን ባርሴሎና በ64 ነጥብ ሲመራ ሪያል ማድሪድ በ60 ነጥብ ሁለተኛ እና አትሌቲኮ በ51 ነጥብ ሦሥተኛ ኾነው ይከተላሉ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here