አዲስ አበባ: የካቲት 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ሥልጠና ምዘና ውድድር “የታዳጊ ስፖርተኞች ልማት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ መልዕክት በአዳማ ከተማ ዛሬ ይጀምራል።
ብቁ ስፖርተኞችን ለማፍራት አላማ ያደረገው ውድድሩ ለስምንት ተከታታይ ቀናት ሲከናወን ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱም ከተማ መሥተዳደሮች የተውጣጡ ከ3 ሺህ በላይ ታዳጊዎች በ15 የስፖርት አይነቶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በውድድሩ ማስጀመሪ መርሐ ግብር ላይ የባሕል እና ስፖርት ሚኒስትሯ ሸዊት ሻንካ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
በቴዎድሮስ ኃይየየሱስ
አሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



