የራሂም ስተርሊንግ ቼልሲን መልቀቅና የኦስካር ቦብ ፉልሃምን መቀላቀል

0
57
ባሕር ዳር፡ ጥር 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ፉልሃም የማንቸስተር ሲቲውን የክንፍ መስመር ተጫዋች ኦስካር ቦብን በ27 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም ከቡድኑ ጋር ተስማምቷል።
ኦስካር ቦብ እግሩ ላይ በደረሰበት ጉዳት ባለፈው የውድድር ዘመን ለቡድኑ ግልጋሎት አልሰጠም ተብሏል። ይህ ተጫዋች አሁን በሙሉ ጤንነት ላይ ሲኾን ፉልሃምን በይፋ ለመቀላቀል መስማማቱ ተዘግቧል።
በሌላ የዝውውር ዜና ራሂም ስተርሊንግ ከቼልሲ ጋር ቀሪ 18 ወራት ቢኖረውም በስምምነት መለያየቱን ቢቢሲ ዘግቧል።
የ31 ዓመቱ ራሂም ስተርሊንግ ከማንቸስተር ሲቲ ቼልሲን የተቀላቀለው እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2022 በ47 ነጥብ 5 ሚሊዮን ፓውንድ መኾኑን ዘገባው ጨምሮ አስረድቷል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here