በኢትዮጵያ ዋንጫ ባሕር ዳር ከተማ ከስልጤ ወራቤ ዛሬ ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋል።

0
153

ባሕር ዳር: 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጥሎ ማለፍ ጨዋታው ቀን 7 ሰዓት በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ይካሄዳል። የስልጤ ወራቤ ቡድን በአንደኛው ዙር መርሐ ግብር የካ ክፍለ ከተማን 2ለ1 አሸንፎ ነው ለሁለተኛው ዙር ጨዋታ የደረሰው።

ጨዋታው ለተመልካች ክፍት እንደሚደረግም ነው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በድረ ገጹ ያስታወቀው።

በኢትዮጵያ ዋንጫ እስካሁን በተደረጉ ጨዋታዎች 11 ቡድኖች ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ፋሲል ከነማ፣ አርባ ምንጭ ከተማ እና መቀሌ 70 እንደርታ በሁለተኛው ዙር ከተሰናበቱት ቡድኖች መካከል ይጠቀሳሉ።

የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ኢትዮጵያን ወክሎ በቀጣይ ዓመት በሚካሄደው የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ ይኾናል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here