የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ራምኬል ሎክ በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የሚሳተፈውን የኑዌር ዞን እግር ኳስ ክለብ ዋና አሠልጣኝ ኾኗል።
ተጫዋቹ የትውልድ ቦታው የኾነውን ክለብ እንዲመራ በመመረጡ ከተጫዋችነት ሕይወቱ በኋላ ወደ አሠልጣኝነት ሙያ ገብቷል። ባለፈው ዓመት አጋማሽ በደቡብ ሱዳን ፕሪሚየር ሊግ ከሚወዳደረው ኤልሜሪክ ጋር ከተለያየ በኋላ ጫማውን መስቀሉ ይታወሳል።
ራምኬል ሎክ በተጫዋችነት ዘመኑ ለቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ፋሲል ከነማ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ድሬዳዋ ከተማ፣ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ሀዲያ ሆሳዕና፣ ሀምበሪቾ ዱራሜ፣ ወልቂጤ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ ተጫውቶ አሳልፏል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_18_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



