የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አምበል እና የባሎንዶር አሸናፊው ሃሪ ኬን ከባየርን ሙኒክ ጋር እስከ 2029 የሚያቆየውን አዲስ የውል ስምምነት ተፈራርሟል። በ2023 ከቶተንሃም በ86 ሚሊዮን ፓውንድ ባየርን ሙኒክን የተቀላቀለው የ33 ዓመቱ አጥቂ፣ የቀደመውን የ4 ዓመት ውል
ለመጠናቀቅ የወራት ጊዜ ብቻ ይቀረው ነበር። ኬን ባለፈው የውድድር ዘመን በባየርሙኒክ ብቻ በ51 ጨዋታዎች 61 ግቦችን በማስቆጠር የክለቡን ክብር ወሰን የሰበረ ሲኾን፣ ባየርን የሊጉን እና የካፕ ዋንጫ ድል እንዲቀዳጅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ስምምነቱን አስመልክቶ ኬን
በሰጠው አስተያየት “በባየርን ሙኒክ ሙሉ በሙሉ የቤት ያህል ምቾት ይሰማኛል። ክለቡን፣ ደጋፊዎቹን እና ሙኒክ ከተማን እወዳለሁ። ምርጥ ቡድን እና ድንቅ አሠልጣኝ አለን፤ የዚህ አካል በመኾኔ በጣም እኮራለሁ” ብሏል። ይህ አዲስ ውል ሃሪ ኬን እስከ 36 ዓመቱ ድረስ በባየርን
የሚያቆየው ሲኾን፣ እስከ ዩሮ 2028 እና 2030 ዓለም ዋንጫ ዋዜማ ድረስ በጀርመን እንደሚቆይ አረጋግጧል። ይህ ውሳኔው በ260 ግቦች የአለን ሽረርን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሪከርድ ለመስበር የቀሩትን 47 ግቦች የማስቆጠር እድሉን ያጠበበ እንደኾነ ተገልጿል።
ሃሪ ኬን በ2025/26 የውድድር ዘመን ለባየርን እና ለእንግሊዝ 73 ግቦችን በማስቆጠር የዓለማችን ኮከብ ተጫዋች በመኾን የባሎንዶር ሽልማት ማሸነፉ ይታወሳል። ቢቢሲ እንደዘገበው በተጨማሪም በቡንደስሊጋው ባደረጋቸው 102 ጨዋታዎች 102 ግቦችን በማስቆጠር ተከታታይ 3 የወርቅ ጫማዎችን እና 2 የሊግ ሻምፒዮናነትን ተቀዳጅቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



