”በሜዳችን ደጋፊዎቻችንን በድል እንክሳለን” የግዮን ንግስቶች

0
77
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታውን ከሀዋሳ ከተማ ጋር አድርጎ በሽንፈት የጀመረው የባህርዳር ከተማ ሴቶች እግር ኳስ ክለብ ሁለተኛ ጨተታውን እሁድ ያደርጋል።
ቡድኑ የመጀመሪያ ጨዋታቸው ክፍተታቸውን የለዩበት እንደነበር እና በጥቃቅን ስህተቶች የተሸነፉበት እንደነበር ገልፀዋል ፡፡
ይሄን እንደመነሻ በመቁጠር ስህተታቸውን አርመን ዝግጅት አድርገናል ብለዋል የቡድኑ አሰልጣኝ እንዳወቀ አጥናፉ እና አምበሏ ማህደር ባየህ።
በሁለተኛ ሳምንት ተጋጣሚያቸው የሆነው ሲዳማ ቡና ልክ እንደ እነሱ የመጀመሪያ ጨዋታውን አዲስ ባደገው ጉለሌ ክፍለ ከተማ ተሸንፎ መምጣቱ የውድድሩን ሶስት ነጥብ ፍለጋ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ቢጠበቅም ባህርዳር ከተማ ሴቶች ግን ሜዳቸውን እና ደጋፊያቸውን ተጠቅመው ድሉን የግላቸው ለማድረግ ተዘጋጅተዋል፡፡
ከአመታት በኋላ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክለቦች በሜዳቸው እንዲጫዎቱ ማድረጉ ለአመታት ከጨዋታ የራቀውን ተመልካች ወደ ሜዳ መልሷል፡፡
በእለተ እሁድ የሚካሄደውን ጨዋታም ደጋፊው ከጎናቸው እንዲሆኑ አሰልጣኝ እንዳወቀ አጥናፉ እና አምበሏ ማህደር ባየህ ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ2ተኛ ሳምንት ጨዋታ ባህርዳር ከተማ ከሲዳማ ቡና እሁድ 9 ሰአት ይካሄዳል።
ዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here