ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ከተደረገው ጨዋታ በኋላ ባሰማው ከባድ አስተያየት በክለቡ ማንቸስተር ዩናይትድ ሊቀጣ መኾኑ ታውቋል።
ማርቲኔዝ አሁን ያለው ሥብሥብ ለታላቁ ክለብ አይመጥንም በሚል ቅሬታውን ማሰማቱን ተከትሎ የመገናኛ ብዙኀን በሰፊው አራግበውታል።
ተጫዋቹ ቅሬታውን ሲያቀርብም የክለቡ ዳይሬክተሮችን ጨምሮ ባለው አካሄድ ቅር መሰኘቱን ገልጿል።
በክረምቱ የዝውውር መስኮት ማይክል ካሪክ በቂ ድጋፍ እንዳልተደረገላቸው መናገሩም በክለቡ አልተወደደለትም። ሊሳንድሮ ክለቡ ለመፎካከር የሚያበቃ ሥብሥብ እንደሌለው፣ 100 በመቶ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት እንደሚያስፈልግ እና ከስፖርት ዳይሬክተሩ ብዙ እንደሚጠብቅ ተናግሯል። እንዲሁም አሠልጣኝ እና ተጫዋቾችን ብቻ መውቀስ ትክክል እንዳልኾነም ገልጿል።
በክለቡ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የተባለውን ይህን ግልጽ ትችት በመሰንዘሩ ማርቲኔዝ ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ ይወሰዳል ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚህ ሁኔታ ጋር ተያይዞ እሑድ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር በሚደረገው ጨዋታ በቋሚነት የመጀመር ዕድሉ አጠራጣሪ ኾኗል።
ከክለቡ ምንጮች እንደተገለጸው ተጫዋቹ ላሳየው ድፍረት የተሞላበት ንግግር እና ክለቡን በአደባባይ በመተቸቱ ቅጣት መቀጣቱ የማይቀር መኾኑ ተረጋግጧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



