
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ታሪክ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሢመሠረት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ባሕል፣ ቱሪዝም እና ማስታወቂያ ቢሮ ውስጥ አንድ መምሪያ ኾኖ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ የክልሉ የዜና ማዕከል ኾኖ ያገለግል ነበር፡፡ ድርጅቱ በ1986 ዓ.ም. የሰው ኃይሉ ቁጥር ከ13 አይበልጡም ነበር፡፡ የሥራ መሳሪዎቹም አገልግሎት የሰጡ፣ ፍጥነት እና ጥራታቸው እምብዛም የኾኑ እና ለሥራ አስቸጋሪ ነበሩ፡፡ በወቅቱ ጋዜጠኞቹም ቢኾኑ የተሰባሰቡት ከኢትዮጵያ ሬዲዮ፣ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተመርጠው የተውጣጡ ናቸው፡፡ በዚያን ጊዜም በድምፅ፣ በፎቶ፣ በጽሁፍ እና በተንቀሳቃሽ ምስል የተዘጋጁት ዘገባዎች በስልክ፣ በፖስታ ቤት፣ በአውሮፕላን ተልከው ለታዳሚያን ይደርሱ ነበር፡፡ ታሕሳስ 7 ቀን 1987 ዓ.ም. ስለአማራ ክልል በጋዜጣ መረጃ ለሚያገኙ የሕትመት ብርሃን የታየበት ቀን ነው፡፡ በወቅቱም “በኩር” የሚል ስያሜ የተሰጠው ጋዜጣ ተመስርቷል፡፡ የስያሜው ቃል ትርጓሜም የመጀመሪያ እንደማለት ነው፡፡ ስምንት ገጽ ያለውን ሳምንታዊ ጋዜጣ ለማተም ጋዜጠኞቹ ጽሁፍ እና ፎቶግራፎችን በሙጫ አጣብቀው፤ ወደ ማተሚያ ቤት በፖስታ ቤት አዲስ አበባ ልከው፤ እንደገና በአውቶብስ ተጭኖ ለዞን እና ወረዳ አንባቢያን ይደርስ እንደነበር ታሪካዊ ዳራው ይዘክራል፡፡ የህትመቱ ይዘቶችም ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ዜና እና ዜና ትንታኔ እንዲሁም አስተማሪ እና አዝናኝ መጣጥፎች ነበሩ፡፡
ዘገባዎች የተቋሙንና የሕዝቡን ክብር የጠበቁ እንዲሆኑ እናደርጋለን፡፡
የዘገባችንን ይዘት አመራረጥ፣ አዘገጃጀትና አቀራረብ ሳቢና ማራኪ እናደርጋለን፤
የታዳሚያችንን ርካታና አመኔታ የሚያሳድሩ ፈጠራዎችን በዘገባ ስራችን ላይ በጥራት እንተገብራለን፤
ዘመናዊ ቴክኖሎጅዎች በመጠቀም የፈጠራ ስራችንን መልዕክት ግልፅ፣ ቀላልና ሳቢ እናደርጋለን፡፡
በፈጠራ የታገዙ ተዓማኒነት ያላቸው ዘገባዎችን በፍጥነትና በጥራት እናደርሳለን፤
ከየትኛውም ወገን የሚቀርቡ አስተያየቶችን ፍትሃዊና ሚዛናዊ በሆነ መንገድ እናስተናግዳለን፡፡ የሕዝብን ጥቅም የሚያስከብሩ ስራዎችን በማከናወን ሕዝባዊ ወገንተኝነትን እናረጋግጣለን፡፡ የሕዝቦችን መብቶችና ነፃነቶችን የሚያስከብሩ ዘገባዎችን በብስለትና በጥልቀት እናቀርባለን፡፡ በሕዝቦች መካከል የእርስ በርስ መደጋገፍና መተባበርን የሚያበረታቱ እሴቶችን እናጎላለን፡፡ የመልካም ስነ-ምግባር መርሆዎችን ለሚተነትኑ ዘገባዎች ትኩረት እንሰጣለን፡፡ ለሕዝብ ልዕልና የሚቆሙ የዘገባ ስራዎችን ቀዳሚ ተግባሮቻችን አድርገን እንዘግባለን፡፡ በምርመራ ዘገባችን ምዝበራና የሀብት ብክነትን በማጋለጥ ተጠያቂነትን እናሰፍናለን፡፡
የቡድን ሥራን በማጎልበት ተጋግዞ የመስራትን መርህ እንከተላለን፤
እርስ በርስ በመማማር ሙያችንን ለማሳደግ እንተጋለን፤
የጋራ ችግርን ተወያይቶ በጋራ በመፍታት መተማመንን እንፈጥራለን፤
ከሌሎች አጋርና ተባባሪ አካላት ጋር በጋራ ሠርተን ውጤት እናመጣለን፤
ለጋራ ውጤት በጋራ መንፈስ እንሰራለን የሚሉ ናቸው፡፡