
ባሕር ዳር፡ መስከረም 26/2013ዓ.ም (አብመድ) የገበታ ለሀገር ፕሮጀክትን አስመልክቶ ለውጭ ሀገር አልሚ ባለሀብቶች ማብራሪያ እየተሰጠ ነው።
ለውጭ ሀገር አልሚ ባለሀብቶች በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ተግባራዊ በሚደረጉት የወንጪ፣ ጎርጎራ እና ኮይሻ (ጨበራ ጩርጩራ) ፕሮጀክቶች ነው ገለፃ እየተደረገላቸው የሚገኘው።
ስለፕሮጀክቶቹ አጠቃላይ ዝርዝር ፍላጎትና ተግባራዊነት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣም ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ እና የጎርጎራ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ፍሰሐ ተገኝ ለባለሀብቶቹ ገለጻ መደረጉን ፋብኮ ዘግቧል።
በገለጻውም ፕሮጀክቶቹ በውስጠቸው ስለሚይዟቸው፣ ስላላቸው የቱሪስት መስህብ እና ተፈጥሯዊ አቅም እንዲሁም ስለሚፈጥሩት የሥራ እድል ተነስቷል።
ባለሀበቶቹም ለፕሮጀክቶቹ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ