
ባሕር ዳር፡ መስከረም 26/2013ዓ.ም (አብመድ) ትምህርት ሚኒስቴር የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል የዩኑቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን በኦላይን ለመፈተን የሚያስችለውን አስፈልጊ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ለባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ጀምሯል፤ በትምህርት ቤቶችም ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችል በቂ የመብራት እና የኔትወርክ አቅርቦት እንዲኖር እየተሠራ መሆኑን ገልጿል፡፡
በኦላይን የሚሰጠው ፈተናም ኩረጃን ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር ከመሆኑም ባሻገር ለወረቀትና ፈተናውን ለማረም የሚወጣውን ወጪና ጊዜ እንደሚቆጥብ ሚኒስቴሩ አመላክቷል፡፡
ቴክኖሎጂው የተለያዩ ሲስተሞች የተጫኑበት ሲሆን ተማሪዎች ፈተናውን በሚወስዱበት ጊዜ የራሳቸው ታብሌት ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ የሚያስችል ሲስተም እንዳለው ተነግሯል።
ፈተናው የሚሰጥባቸው ታብሌቶችም በቅርቡ ለተማሪዎች እንደሚሠራጩ የትምርት ሚኒስቴር በማኅበራዊ ገጹ አስታውቋል።
ተማሪዎችም ከቴክኖሎጂው ጋር እንዲተዋወቁ ከሦስት ሣምንት ያላነሰ ጊዜ የሚሰጣቸው ሲሆን ምንም ሳይጨናነቁ ለፈተና እንዲዘጋጁ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ