ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በሚገነባበት አካባቢ ከተፈቀደላቸው በረራዎች ውጭ ለሌሎች በረራዎች የአየር ክልሉ ዝግ መደረጉ ተገለጸ፡፡

213

ባሕር ዳር፡ መስከረም 25/2013ዓ.ም (አብመድ) በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አካባቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ የአየር ክልል ከተፈቀደላቸው በረራዎች ውጭ ለሌሎች በረራዎች ዝግ መደረጉንና መከልከሉን የኢትዮጵያ ሲቪል አቬዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ። የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሺመልስ ክብረአብ ዛሬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በሚገኝበት የኢትዮጵያ የአየር ክልል ውስጥ ለመብራር ከባለስልጣኑ ልዩ ፈቃድ ማግኘት ግዴታ ነው።

ከባለስልጣኑ ልዩ ፈቃድ ያላገኘ ማንኛውም የሲቪልም ሆነ ወታደራዊ በረራ ማድረግ እንደማይቻል የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ክልከላው በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚመለከተው አካል ሁሉ እንዲያውቀው መደረጉን አብራርተዋል።

ማንኛውም አገር ትልልቅ ፕሮጀክቶችና መሰል ሥራዎች በሚያከናውንባቸው አካባቢዎች ተመሳሳይ ክልከላ እንደሚያደርግ የተናገሩት አቶ ሺመልስ በኢትዮጵያም በኩል የግድቡን ደኅንነት ለማረጋገጥ ሲባል ክልከላው ተግባራዊ መደረጉን ገልጸዋል።
እንደ ኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ዘገባ ከባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ልዩ ፈቃድ የሚያገኙ በረራዎች ብቻ በአየር ክልሉ መንቀሳቀስ እንደሚችሉና ይህም ተግባራዊ እየተደረገ እንደሆነ አቶ ሺመልስ አስታውቀዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየጥሬ ጨው አመራረት፣ ማቀነባበርና የግብይትና አጠቃቀም ሂደት ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።
Next articleበሁለት ወራት ብቻ ለ74 የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን ከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡