አሜሪካ ለማሊ የሽግግር መንግሥት ድጋፍ ሰጠች፡፡

162

ባሕር ዳር፡ መስከረም 24/2013ዓ.ም (አብመድ) አሜሪካ ማሊ የሽግግር መንግሥት መመሥረቷን ተከትሎ “ወደ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ለመመለስ የመጀመሪያ እርምጃ” ስትል ገልፃለች ፡፡

በያዝነው የመስከረም የሽግግር ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመው ጡረታ የወጡት ኮሎኔል ፕሬዝዳንት ባህ ንዳው አንጋፋውን ዲፕሎማት ሙክታር ኦዋን ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው ሹመዋል፡፡

ጊዚያዊው የሽግግር መንግሥቱ ለ18 ወራት እንደሚቆይ ታውቋል፡፡ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ሞርጋን ኦርታጉስ “የሽግግር መንግሥቱ በምዕራብ አፍሪካ ግዛቶች የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ (ኢኮዋስ) ውስጥ በ18 ወራት ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማካሄድን ጨምሮ የገባው ቃልኪዳን እንዲያከብር እንጠይቃለን” ብለዋል ፡፡

የሽግግር መንግሥቱ ሙስናን በመዋጋት የምርጫ ሂደቶችን እንዲያስተካክልም በመግለጫው አሳስቧል ፡፡

ቃል አቀባዩ “መንግሥት የሰብዓዊ መብቶችን እንዲያከብር እና እነዚህን የመብት ጥሰቶች በክልል የፀጥታ ኃይሎች ለማስቀረት እንዲሁም ጥሰቶች በሚከሰቱበት ጊዜ ተጠያቂዎችን እንዲመረምር እና ተጠያቂ እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን” ብለዋል፡፡

በግርማ ተጫነ

Previous articleየበረሃ አንበጣ መንጋው ከየአገራቱ የሚመጣ ስለሆነ አንድ አገር ወይም አህጉር ብቻውን የሚከላከለው ስላልሆነ አገራት በጋራ ርብርብ ሊያደርጉ እንደሚገባ የግብርና ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡
Next article40ኛው የለንደን ማራቶን በሴቶች በኬንያዊዋ ብሪጅ ኮስጌ የበላይነት ተጠናቅቋል፡፡