
ባሕር ዳር፡ መስከረም 22/2013ዓ.ም (አብመድ) በምሥራቅ አማራ የተከሰተውንና ጉዳት ያደረሰውን የበረሃ አንበጣ መንጋ ለመከላከል በርጭት ሥራ ላይ የነበረችው ሄሊኮፕተር ዛሬ መስከረም 22 ቀን ከረፋዱ 4:30 ላይ በወረዳው 014 ቀበሌ ተከስክሳለች፡፡ ሄሊኮፕተሯ የተከሰከሰችው በቴክኒክ ብልሽት ነው ተብሏል፡፡
የሄሊኮፕተሯ አብራሪ በሰመራ ሆስፒታል የሕክምና እርዳታ እየተደረገለት ሲሆን በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል፡፡
ሄሊኮፕተራ በተከሰከሰችበት ስፍራ የአብራሪውን ሕይወት ለመታደግ ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል፡፡
የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አበባው ጌቶን ጨምሮ የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊና የወረባቦ ወረዳ አስተዳዳሪ የአደጋውን ስፍራ ተመልክተዋል፡፡ አርሶ አደሮች ላደረጉት ትብብርም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የሄሊኮፕተሯ መከስከስ በአካባቢው ያለውን የበረሃ አንበጣ መንጋ በመከላከሉ ሥራ ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጥራልም ተብሏል፡፡
ዘጋቢ፦ አሊ ይመር -ከወረባቦ አራባቲ