
በተያዘው የ2013 በጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ እንደሚሠራ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ገለፀ፡፡
ምክር ቤቱ ባዘጋጀው የምክክር ጉባኤ ላይ እንደተገለፀው የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ አንስቶ የኅብረተሰብ ድጋፍ ከፍተኛ እንደነበር አስታውሷል፡፡ በ2012 በጀት ዓመት ከ29 ሚሊዮን ብር በላይ ከኆብረተሰብ ድጋፍ መደረጉን የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታገል ቀኑብህ ተናግረዋል፡፡
በተያዘው በጀት ዓመትም ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ለማሰባሰብ የተለያዩ ሥራዎች ይሠራሉ ብለዋል፡፡
የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎችም ጽሕፈት ቤቱ እያከናወናቸው ያሉትን ተግባራት በቀጣይ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት፡፡
በምክክር መደረኩ ከፌዴራልና ከክልል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ኃላፊዎች መገኘታቸውን ኢብኮ ዘግቧል።