
ባሕር ዳር፡ መስከረም 22/2013ዓ.ም (አብመድ) አመልድ ጆንስ ሪግ ዋሽ ፕሮጀክት በምሥራቅ ጎጃም ዞን ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከላከል የሚውል ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። ድጋፉ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል፣ ፈሳሽ ሣሙና፣ ብርድ ልብስ እና ፍራሽ ሲሆን በዝቅተኛ ገቢ ለሚኖሩ ወገኖች የሚሰጥ ነው።
ድጋፉን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ በሥሩ ለሚገኙ አምስት ወረዳዎች የሚያሠራጭ ይሆናል። አመልድ ጆንስ ሪግ ዋሽ የለገሰው ድጋፍ 4 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት እንዳለው ተመላክቷል።
ዘጋቢ፡- የኔነህ ዓለሙ -ከደብረ ማርቆስ